Latest Post * ለከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ * የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የድህረ ገጽ አገልግሎት መጠቀም ጀመረ። * የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የመረጃ ዲጂታላይዜሽን ስራ ተሰርቷል

እንኳን ወደ ድህረገጻችን የማስታወቂያ እና ተዛማጅ ጉዳዮች መፈለጊያ ገጽ በደህና መጡ ድህረገጻችንንም ስለጎበኙ እናመሰግናለን

ለከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ

ዓመታዊ የሊዝ ክፍያ ያልከፈላችሁ ቅጣትና ወለድ ታስቦ እስከ ሰኔ 30/10/2017 ዓ/ም እንድታጠናቅቁ እያሳሰብን ከሰኔ 30 በኋላ በህግ አግባብ የምንጠይቅ መሆኑን አናሳስባለን የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት     

  21-06-2025 16:14pm

የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የድህረ ገጽ አገልግሎት መጠቀም ጀመረ።

የድህረ ገጽ አገልግሎትን በመጠቀም ለህብረተሰባችን ልዩ ልዩ አገልግሎት እንሰጣለን ከህብረተሰቡ ሀሳብ አስተያየት እንቀበላለን የባለ ይዞታወች መለያ እንፈጥራለን ባለ ይዞታዎች በመለያቸው በመግባት የይዞታ ፋይላቸውን ማውረድ ይችላሉ ከፋይላቸውጋ ያለውን እንቅስቃሴ በቀላሉ መከታተል የሚችሉበትን መንገድ ፈጥረናል የማስታወቂያ አገልግሎትም በዚሁ ድህረገጽ አካተናል።

  20-06-2025 21:41pm

የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የመረጃ ዲጂታላይዜሽን ስራ ተሰርቷል

በግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የይዞታ ፋይልን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል የመረጃ ቋት አስገብቷል። ለዚህም ስራ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በመሳተፍ ስራው የተፋጠነ ሲሆን ተሰርቶ ሲጠናቀቅም አገልግሎቱ በሚገባ ጠቃሚ መሆኑን በመረዳት ስራውን እንስራ በሚል ሀሳብ በቁርጠኝነት በመነሳት የፋይል ማዘመኑን ስራ በስኬት ተጠናቋል     

  20-06-2025 21:36pm

1 ራዕይ

ለኗሪዎችና ለኢንቨስትመንት ምቹ, ጽዱ ውብ እና አረንጓዴ ሙጃ ከተማን በመፍጠር እና በኢኮኖሚያዊ በማህበራዊ እና በሁለንተናዊ መልኩ የነቃ የከተማ ማህበረሰብ መገንባት     

  20-06-2025 15:57pm

2ተልዕኮ

የከተማችን የገቢ አቅም በማሳደግ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን በመከላከል ዘመናዊ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ስርዓት በመዘርጋት እና የከተማ ግብርና በማስፋፋት ለከተማችን የሚመጥን መሰረተ ልማት በመዘርጋት ለወጣቱ የስራ ዕድል በመፍጠር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ     

  20-06-2025 15:56pm

Social media contacts