👤👤Staff
Home About Us Main point Service Job Vacancy Materials Comment

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!

ℹ የግዳን ወረዳ ርዕሰ መዲና ሙጃ ከተማ ታሪክ

የሙጃ ከተማ ታሪክ በአጭሩ ሲታይ
የግዳን ወረዳ ርዕሰ መዲና ሙጃ ከተማ የተመሰረተችው በ1902 ዓ.ም ሲሆን ሙጃ የሚለው ስም የመጣው ሙጃ የሚባል ሳር በብዛት የሚበቅልባት አካባቢ በመሆኗ ሲሆን ከጎንደር ወረታ ጋይንት የሚመጡ የጨው ነጋዴዎች ቆቦ ጨው ለመነገድ ሙጃን አቋርጠው ይሄዳሉ በዚህ ጊዜ ነጋዴዎቹ ማደሪያችን ያች ሙጃ ሳር የሚበቅልባት ቦታ ነች ብለው ከሁለቱም ቦታ ሲመላለሱ ማደሪያቸው አድርገዋት ስለነበር በዚህ ምክንያት ሙጃ ብለው አወጡላት፡፡
ሙጃን ለመጀመሪያ ጊዜ የቆረቆሯት ሰው ደጃች ሀይሉ ወ/ኪሮስ ይባላሉ፡፡ ይህ ሰው በመጀመሪያ ቤት አድርገው የቆረቆሩበትም በአሁኑ ጊዜ የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን የተሰራበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ሰው በ1913 ከሞተ በኋላም ቤተሰቦቹ ቦታውን ይዘውት ይኖሩበት ነበር፡፡ ከዛም በመቀጠል ሙጃ ከመቆርቆር አልፋ ወደ ከተማነት ስትሻገር ይህ ቦታ የከተማዋ የቀበሌ ጽ/ቤት ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡ ሙጃ ወደ ወረዳነት ስትለወጥ ቦታው የወረዳ ፍ/ቤት፣ ፖሊስ ጽ/ቤት የማ.ክ.ሰ.ማ የእጅ ስራ ማሰልጠኛ በመሆን አገልግሏል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታም ሙጃ መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ተሰርቶበት እያገለገለ ይገኛል፡፡
በ1928 ዓ.ም ሙጃ ወደ ወልዲያ መውጫ ልዩ ቦታው ዙሮበር የሚባል ቦታ ላይም ጣልያን ካምፕ ሰርተው ይኖሩበት ነበር፡

🔭  ራዕይ

ለኗሪዎችና ለኢንቨስትመንት ምቹ, ጽዱ ውብ እና አረንጓዴ ሙጃ ከተማን በመፍጠር እና በኢኮኖሚያዊ በማህበራዊ እና በሁለንተናዊ መልኩ የነቃ የከተማ ማህበረሰብ መገንባት

🎯  ተልዕኮ

የከተማችን የገቢ አቅም በማሳደግ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን በመከላከል ዘመናዊ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ስርዓት በመዘርጋት እና የከተማ ግብርና በማስፋፋት ለከተማችን የሚመጥን መሰረተ ልማት በመዘርጋት ለወጣቱ የስራ ዕድል በመፍጠር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ

loading

👨‍💻  አቶ ዘመድ ቢረዳ


የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ