👤👤Staff
Home About Us Main point Service Job Vacancy Materials Comment

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!

የሙጃ ከተማ መሰረተ ልማትን የበለጠ ለማስፋፋት እየሰራሁ ነዉ ሲል የሙጃ መሪ መዘጋጃ ቤት ገለጸ

05-04-2026 17:29pm

ሙጃ፦ ቀን 26/7/2017ዓ.ም (ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን)
ሙጃ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉ የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የመንገድ ዳር መብራት፣የጎርፍ መፋሰሻ ቦይ ግንባታ እና የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ መለየት በዋናነት የሚጠቀሱ መሆኑን በመጠቆም በዕቅድ ተይዘዉ ያልተገነቡ ሁሉንም የመሰረተ ልማት ስራዎች ለማከናወን እና በሰፊዉ መሰረተ ልማት ያልተዳረሰበቻዉ የከተማዋ አካባቢዎችን ለማዳረስ እንዲሁም የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ስራ ለመስራት በሚፈለገዉ ልክ ገቢ አለመሰብሰቡ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ሲሉ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ ገልፀዋል፡፡
ህገ-ወጥ ግንባታን ከማፍረስ አኳያ በቁርጠኝነት እርምጃ እንደሚወሰድ የተናገሩት ዋና ስራ አስኪያጁ ለመሰረተ-ልማት ዋናዉ አስፈላጊ ጉዳይ ገቢ በመሆኑ በተለያየ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ አካላት የሚጠበቅባቸዉን ክፍያ በፍቃደኝነት መክፈል እንደሚገባቸዉ አስገንዝበዋል፡፡
አክለዉም የሙጃ ከተማን ፅዳት ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዉ ስራ እስኪጀምር ድረስ የከተማዋ ነዋሪዎች ቆሻሻን ባልተፈለገ ቦታ እንዳይደፋ በማሳሳብ ለከተማዋ እድገት መንግስት ሰራተኛዉም ሆነ ማንኛዉም የማህበረሰብ ክፍል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

loading

ይህ መረጃ 21 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form