መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 05-04-2026 17:33pm

በግዳን ወረዳ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የዲጂታላዝድ ሲስተም መጀመሩን ገለጸ

ሙጃ ፡ ቀን 2/11/2017ዓ.ም (ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን) በግዳን ወረዳ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት እንዳስታወቀዉ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ እና አስተዳደር የሚያስፈልግ በመሆኑ የዲጂታላዜሽን ስራ የተጀመረ ሲሆን በዚህም ለበርካታ ዓመታት በማንዋል ይሰራ የነበረዉን የወረቀት ስራ ወደ ዲጂታላይዜሽን በመቀየርና በማዘመን 2512 ይዞታዎች ሶፍትዌር ላይ መጫናቸዉን የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ አሳዉቀዋል፡፡ የመሪ መዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አክለዉ እንደተናገሩት ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጅን መጠቀምና መረጃዎችን ዲጂታላይዝ ማድረግ ደንበኞች በየትኛዉም ጊዜና ቦታ ፋይላቸዉን በዕጅ ስልካቸዉ እንዲከታተሉ ፣አዳድስ ፋይሎች ሲቀነሱና ሲጨመሩ መረጃ እንዲያገኙ፣ለሰነድ ደህንነትና ቁጥጥር እንዲሁም በተፍጥሮና ሰዉ ሰራሽ አደጋ መረጃ እንዳይጠፋ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለዉ ገልፀዉ ይህንን የዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ በማድረግ የከተማዋን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንደሚፈታ አስገንዝበዋል፡፡ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቡድን መሪ አቶ በላይ ደርቤ በበኩላቸዉ መሬት ዉድ ሃብት መሆኑን ገልጸዉ የዲጂታላይዜሽን ሲስተም ባለሙያዉ በቀላሉ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት እንዲችል፣ከዘረፋና ከህገወጥ ደላሎች መሬትን ለመጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ አቶ በላይ ደርቤ አያይዘውም አገልግሎትን ዲጅታላይዝ ለማድረግ በዋናነት የኢንተርኔት ፣የኮምፒዉተር እና ኔትወርክ ኬብል መሟላት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ይህ ዘገባ የተነበበው 5ጊዜ ነው

Comment Form