05-04-2026 17:36pm
የከተሞችን እድገት ለማፋጠን ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ስራዎች መከናወናቸዉን የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ
ሙጃ፡ ቀን 15/11/2017 ዓ.ም (ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን) የወረዳዉ ከተማና መሰረተ-ልማት ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ ተቋሙ 1 መሪ መዘጋጃ ቤት እና 2 ታዳጊ ከተሞችን (ሙጃ፣ ወንዳች እና ደንሳ) ከተሞችን እያስተባበረ የሚመራ ተቋም መሆኑን በመጠቆም በ2017 የጎርፍ መቀልበሻ ተፋሰሶች ፣ የመብራት ማስፋፊያ ስራዎች ፣የሆስፒታል ግንባታን ጨምሮ ዋና ዋና መሠረተ ልማቶች መሠራታቸውን የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ-ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ ቸኮለ አሳዉቀዋል፡፡ ኃላፊዉ አክለዉ እንደገለፁት እነዚህ ግንባታዎች የተገነቡት ከመንግስት እና ከተራድኦ ድርጅቶች በተገኘ በጀት ነዉ ያሉ ሲሆን ለደንሳ ታዳጊ ከተማ መብራት ማስፋፊያ 6 .4ሚሊዮን ብር በላይ ፣በሙጃ ከተማ ለተገነባዉ የጎርፍ መቀልበሻ ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ ፣ ለሙጃ ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ለጎርፍ መፋሰሻ 1.1ሚሊዮን ብር ወጭ መደረጉን ገልፀዉ በአጠቃላይ ከ10ሚሊዬን ብር በላይ በማውጣት መሠረተ ልማቶቹ የተሰሩ ሲሆን ለጎርፍ መቀልበሻ ግንባታዎች የክልሉ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና አደጋ መከላከል ሰፊ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ በመጨረሻም የእነዚህ መሰረተ ልማቶች መጠናቀቅ የሙጃን ከተማ ነዋሪዎች እና የወረዳውን ህዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።
