መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 05-04-2026 17:38pm

የግዳን ወረዳ ከተማናመሠረተ ልማት ፅ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ሙጃ ፦ ቀን 08/02/2017 (የግዳን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን) የወረዳው ከተማናመሠረተ ልማት ጽ/ቤት የ2016 ዓ,ም አፈፃፀም እና የ2017 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገ ሲሆን ፤ በመድረኩ የግዳን ወረዳ አስተዳዳሪ ፤ አጋር የወረዳ አመራሮች ፤ የሙጃ መሪ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆችናባለሙያዎች ፤ የደንሳናወንዳች ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆችናባለሙያዎች፤ የቀበሌ አመራሮች እንድሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል። መድረኩን የከፈቱት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው በአስተላለፉት መልእክት የከተማናመሠረተ ልማት ተቋሙ በስሩ ያሉትን መሪናታዳጊ መዘጋጃ ቤቶች በመደገፍናበመከታተል በ2016 ዓ,ም ለአስመዘገበው አንፃራዊ ለውጥናአፈፃፀም እውቅና ሠጥተው በቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸውን ተግባራት ቆጥሮ በመያዝ አጋር አካላቱ የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበው ፤ ለሠላም የድርሻችንን በመወጣት ወደ ልማታችን ለመመለስ ጥረት ማድረግ ይገባል ብለዋል። በአቶ ዘመድ ቢረዳ የሙጃ መሪ ማዘጋጃቤት ዋና ስራ አስኪያጅ የተቋሙ የ2016 ዓ,ም አፈፃፀም እንደመነሻ ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ፤ የ2017 በጀት አመት እቅድ በግዳን ወረዳ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ፕላነር ባለሙያ በአቶ ተመስገን ብርሃን ቀርቦ ከተሳታፊዎች በርካታ ሀሳብ ተነስቶ ውይይት ተደርጓል። በመድረኩ ማጠቃለያ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው ፤የወረዳው ከተማናመሠረተ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሠማኝ ቸኮለ እና የሙጃ መሪ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦች ምላሽ በመስጠት ሁሉም አካል ለከተሞች እድገትናመስፋፋት የድርሻውን እንዲወጣ ጠቁመው፤ ተቋሙ በ2017 በጀት አመት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ከ37 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ የሚጠበቅበት በመሆኑ የ3ቱም ከተሞች ኗሪዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተግባራት እርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው እና ውብ፣ማራኪናአረንጓዴ ተፈጥሮን የተላበሰ ከተማ ለመፍጠር ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እዲወጡ የጋራ የልማት ጥሪ አቅርበዋል። በመጨረሻም ለአጋር ተቋማት ፤ ለባለድርሻ አካለት፤ለመዘጋጃ ቤት መሪዎች ፤ ለባለሙያዎች ሰፊ የማበረታቻ ስነ_ስርአት በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል።

ይህ ዘገባ የተነበበው 4ጊዜ ነው

Comment Form