ለረጅም አመታት በማህበር ተደራጅተው የነበሩ የቤቶች ማህበር የቤት መስሪያ ቦታ ርክክብ የተደረገላቸው መሆኑን በግዳን ወረዳ የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ገለጸ
02-05-2026 17:47pmለረጅም አመታት በማህበር ተደራጅተው የነበሩ የቤቶች ማህበር የቤት መስሪያ ቦታ ርክክብ የተደረገላቸው መሆኑን በግዳን ወረዳ የሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ገለጸ
ቀን 20/10/2016 ዓ.ም(ግዳን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን) የግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ እንደተናገሩት የ2016 ዓ/ም የመኖሪያ ቦታ ምሪት የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም እንደ ወረዳ ከሚመለከተው አጋር አካላት ጋር እልህ አስጨራሽ ስራዎችን በመስራትና ውይይት በማድረግ እንዲሁም ለችግሮች መፍትሄ በመስጠት ከይዞታ የሚነሱ 328 አርሶ አደሮች እና በ27 ማህበር የተደራጁ 519 የመኖሪያ ቦታ የሌላቸው ግለሰቦች በአጠቃላይ 847 ህብረተሰብ የመኖሪያ ቦታ ባለቤት ማድረግ የተቻለ መሆኑን ገገልጸው ተመሪዎች በፕላን ምድቡ መሰረት የመኖሪያ ቤቶችን እንዲገነቡ በተቋማቸው ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
የመኖሪያ ቦታ ባለቤት የሆኑት ተመሪዎችም በበኩላቸው ማህበሩ ከተደራጀ ጀምሮ የሚጠበቅባቸውን ገንዘብ በመቆጠብ የቦታ ባለቤት መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸው ቦታውን ለማግኘት ብዙ ውጣ ውረድ ቢኖረውም የሚመለከታቸውየመንግስት አካላት ላደረጉት ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በተመሳሳይ የመሬት ባለይዞታዎችም እንደተናገሩት በይዞታ መሬታቸው ላይ ለልጆቻቸው እና ለራሳቸው የቤት መስሪያ ቦታ ተጠብቆላቸው በቀሪ ቦታቸው ካሳ እንደተከፈላቸው ገልፀው፤የካሳ ክፍያውን በተመለከተአነስተኛ መሆኑን አመላክተው የተሰጣቸውን የካሳ ክፍያ በአግባቡ በመጠቀም ወደ ስራ እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡
የግዳን ወረዳ ም/ዋና/አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው እንደገለጹት የ2016ዓ/ም የመኖሪያ ቦታ ምሪት ከሚመለከታቸው አጋር መስሪያ ቤቶች ጋር የጋራ በማድረግ በማስተባበር በመገምገም ለችግሮች መፍትሄ በመስጠት ተመሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ መሆኑን ጠቁመው በዚህም መሰረት የቦታ ምሪቱ ፖሊሶችን፣ልዩ ሀይል አባላትን፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን፣የመንግስት ሰራተኞችንናሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካተተ መሆኑን ተናግረው፤ይህን ስራ ለመስራት ተመሪዎች እና አርሶ አደሮች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች ቢኖሩም ከሚመለከተው አጋር አካላት ጋር የጋራ በማድረግ ችግሩን መፍታት እንደተቻለ ጠቁመው፤ በቀጣይ በከተማው ውስጥ የሚኖረው አብዘሀኛው ህብረተሰባችን ቤት የሌላቸው በመሆኑ የከተማውን ፕላን በማሻሻል የቦታ ምሪቱ እንድቀጥል ለማድረግ፤ህ/ቦቹም በማህበር ተደራጅተው እየቆጥቡ እና ተገቢውን የህብረት ስራ ማህበራት መመሪያን ጠብቀው የተደራጁ አካላትን ለማሳተፍ እቅድ ይዘው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡






