05-04-2026 18:11pm
በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የ2016ዓ.ም የአሸንድየ በዓል በድምቀት ተከበረ
በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የ2016ዓ.ም የአሸንድየ በዓል በድምቀት ተከበረ ነሐሴ 17/12/2016ዓ.ም (የግዳን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን) በዚህ የበዓል አከባበር ፕሮግራም የወረዳ አመራሮች፣የሃይማኖት አባቶች፣ወጣቶች እና ልጃገረዶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ ባለድርሻ አካለት ሲሆን በፕሮራሙ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የግዳን ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌዉ እንደተናገሩት የአሸንድዬ በዓል የሴቶች እህቶቻችን የነፃነት በዓል እንደመሆኑ መጠን ይህን በዓል ስናከብር ባህላችንን በመጠበቅ ለተተኪዉ ትዉልድ ማስተላለፍ እንደሚያሥፈልግ መሆኑን ጠቁመዉ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን የሁሉም ርብርብ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ለሠላም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ የግዳን ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባህል እሴቶችና ኢንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪ ወ/ሮ አስረበብ አየነዉ በበኩላቸዉ ይህ በዓል በወረዳችን ለ4ኛ ጊዜ በህላችን ለሰላማችን እና ለአንድነታችን በሚል መሪ ቃል የተከበረ በዓል ነዉ ያሉ ሲሆን በዓሉ በተገቢዉ መንገድ እንዲከበር እና ትዉፊቱን ጠብቆ ለትዉልድ እንዲተላለፍ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸዉን ገልፀዉ የአሸንድዬ በዓል ለቀጣይ ከዚህ በተሸለ መልኩ እንዲከበር ማህበረሰቡ የኔነት ስሜት ኖሮት አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ቡድን መሪዋ አክለዉ እንደ ጽ/ቤት ግንዛቤ መፍጠር እና ባህሉን ማስረፅ እንደሚጠበቅ ገልፀዉ አስተዳደር ም/ቤቱ የባህልና ቱሪዝምን የበጀት ችግር መፍታት እንዳለበት፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣የሃይማኖት አባቶች የሚጠበቅባቸዉን መደገፍ እንዳለባቸዉ እንዲሁም ወላጆች ስለ ባህላቸዉ እንዲያዉቅ ማስተላልፍ፣ወጣቱ ደግሞ ባህሉን ጠያቂ እና አዋቂ እንዲሁም ቅርስን ጠባቂ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ሙጃ!!!!
